=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
አሏህ በአንተ ላይ የዋለቸውን ውለታዎች አስባቸው በሁሉም አቅጣጫ አካበውህ ታገኛቸዋለህ።
----.•´¯)(¸.•´¯)(¸.•´------
አል-ቁርአን 14:34
----`•._)(¯`•._)(¯`•.-----
"የአሏህንም ፀጋ ብትቆጥሩ አትዘልቁትም"
ለአካልህ ጤንነትን፣ምግብና ልብስን፣አየርና ውሃንም ሰቶሀል።ሳታስተውለው ህይወት በእጅህ ናት፤ ሳታስበው ደግሞ ዱንያ በደጀህ ናት።
----.•´¯)(¸.•´¯)(¸.•´------
አል-ቁርአን 31:20
----`•._)(¯`•._)(¯`•.-----
"ፀጋዎቹም ግልፅም ድብቅም ሲሆኑ የሞላችሁ መሆኑን አታዩምን።"
√ ሁለት ዐይኖች አሉህ።ምላስና ከንፈሮች፣ሁለት እጆችና እግሮችም አሉህ።ታዲያ የትኛውን የጌታህን ፀጋ ታስተባብላለህ?
√ ብዙ እግሮች በተቆረጡበት ዘመን በሁለቱም እግሮችህ መራመድ መቻልህ ቀላል ነገር ነውን? ህመም ብዙ ሰዎችን እንቅልፍ ነስቶአቸው ሳለ ያለምንም ችግር መተኛት መቻልህ፤የለት ጉርሻቸውን ያጡ እና ንፁህ ውሃ አጥተው በሽታ የሚያስከትለውን አንዳንዴም ለሞት የሚዳርገውን ድፍርስ ውሃ የሚጠጡ ሰዎች በበዙበት ዘመን ሆድህን በጣፋጭ ምግቦች መሙላትህ አና ቀዝቃዛና ንፁሁን ውሃ መጠጣትህ የሚናቅ ነውን?
መስሚያህን አስብ ከድንቁርና ድንሃልና።ማያህን አስብ ከአይነ ስውርነት ድነሃልና።ቆዳህንም ተመልከት ከለምፅና ከቁምጥ ርቃሃልና።
√ አንድ ዓይንህን ተራራ በሚያህል ወርቅ መለወጥ ትፈልጋለህን?
√ መስሚያ ጃሮህንስ ኮረብቶችን በሚመዝን ብር መሸጥ ትሻለህን? ምላስህን ውብና ድንቅ በሆነ ቤተመንግስት ቀይረህ ዱዳ ሆነህ መኖርን ትመርጣለህን?
√ እጅህን በሉልና በከበሩ ድንጋዮች ለውጠህ እጅ አልባ ሆነህ መኖር ያምርሃልን?
አላወክም እንጂ እጅግ ብዙ በሆኑ ጸጋዎችና በርካታ ችሮታዎች ውስጥ ተዘፍቀሃል።ትኩስ ዳቦ፣ቀዝቃዛ ውሃ፣ቆንጆ እንቅልፋ፣የተሟላ ጤንነትን ወዘተ ኖረውህ ያጣኸው ያስጨንቅሃል! የደስታ ቁልፍ በእጅህ እያለ እልፍ አዕላፍ ፀጋዋችን መልካም ነገሮችና ችሎታዎች እያሉህ አንዴ ለደረሰብህ ኪሳራ ትጠበባለህ።
----.•´¯)(¸.•´¯)(¸.•´------
አል-ቁርአን 51:21
----`•._)(¯`•._)(¯`•.-----
"በነፍሶቻችሁም ውስጥ ምልክቶች አሉ ታዲያ አትመለከቱምን"
በአንተ ላይ፣በቤተሰቦችህ፣በቤትህ፣በጔደኞችህ እና በዙሪያህ ባሉ ነገሮች ላይ የፈሰሱ ፀጋዎችን አስባቸዉ።
አስብና አመስግን!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|